News detail
ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል እና ኒውሮ ሳይንስ ተቋም የጥራት ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን በመተግበር ቀጣይነት ያለው የህክምና አገልግሎት ጥራት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑ ተገለፀ።
የኢንፌክሽን መከላከል እና የታካሚ ደህንነትን በተመለከተ ሁለት የጥራት ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን /Quality Improvement Projects/ታህሳስ 16/5/2016 ዓ.ም በሆስፒታሉ ግቢ አስመርቋል።
ፕሮግራሙ በህፃናትእና አዋቂዎች ተኝቶ ህክምና ክፍሎች የጤና ባለሙያዎችን የእጅ ንፅህና አጠባበቅ እና የቆሻሻ አወጋገድን በማሻሻል ላይ ያተኮረ ሲሆን ሆስፒታሉ ቀጣይነት ያለው መሻሻል ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል በፕሮግራሙ የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉቀን ስፋየን ጨምሮ ሌሎች የማኔጅመንት አመራሮች እና የክብር እንግዶች የተገኙ ሲሆን የፕሮጀክቱን አፈፃፀም የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያ የሆኑት አቶ ኢብ ራሂም እሸቴ እና ከአዲስ አበባ ጤናቢሮ የፕሮጀክቱ ተሳታፊ የነበሩት ባንች አምላክ አስማረ አቅርበው የስኬት ስልቶችንም አመላክተዋል።
የፕሮጀክቶችን ውጤት ዘላቂ ለማድረግ እና መስፋፋት እንዲያስችል አሳታፊ ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ ዶ/ር ሙሉ ቀን ተስፋየ የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ እንደገለፁት የጥራት ማሻሻያ ፕሮጀክቶች በጤና አጠባበቅ ላይ ያላቸውሚና ወሳኝ መሆኑን አፅንዖት ሰጠው ያብራሩ ሲሆን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለማድረግም ቃል ገብተዋል።
በመጨረሻም በፕሮግራሙ ቁልፍ አስተዋፅዖ ያደረጉ ሰዎች እውቅና እና የምስጋናየምስክር ወረቀት የተሰጣቸውሲሆን የፕሮጀክቱን አውንታዊ ተፅዕኖ ለማጠናከር እና ለማስፋት ጉብኝት በማድረግ ተጠናቋል።
Latest News
Eka Kotebe Hospital Provides Emergency Medical Services at the 2nd Africa Climate Summit
Posted On: 8 Sep 2025
Congratulations, Dr. Megersa Alemu!
Posted On: 29 Aug 2025
An oxygen production center is under construction at Eka Kotebe Hospital.
Posted On: 17 Aug 2025
.png)