News detail
የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ህብረተሰብ ተሳትፎ በጎፍቃድ ማስተባበሪያ ጽፈት ቤት በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ለታካሚዎች ድጋፍ አደረጉ
የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አመራርና አባላት በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ጉብኝት አደረጉ ዓላማውም በሆስፒታሉ ለሚገኙ ታካሚዎች ድጋፍ በማድረግ፣ አብሮነትንና አጋርነትን ማሳየት እንደሆነ ተገልጿል።
የወረዳ 9 የህብረተሰብ ተሳትፎ በጎ ፍቃድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘመነ አስማረ እንደተናገሩት፣ ይህ ተግባር ለታካሚዎች ተስፋንና ድጋፍን ለመስጠት ያለመ እንደሆነና ከታካሚዎች ጎን በመሆን ተስፋን ለመስጠት ግብ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉቀን ተስፋዬ በበኩላቸው፣ ክፍለ ከተማው የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ባደረጉት ጉብኝት መደሰታቸውን ገልጸው፣ ሆስፒታሉ በማንኛውም ጊዜ የነሱን የበጎ ድጋፍ በአብሮነት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም ሆስፒታሉ ከየካ ክፍለ ከተማ እና ወረዳ አደረጃጀት እንዲሁም ከማህበረሰብ ጋር በቅርበት መስራቱ መልካም ባህል እየሆነ መምጣቱን በመናገር የማህበረሰብ ተኮር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል ።
በመጨረሻም የበጎ ፈቃድ ተግባራት እንዲበረታቱ ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ አበባ:- መጋቢት 5/2017 ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ
የላቀ አገልግሎት አርማችን!
Latest News
Eka Kotebe Hospital Provides Emergency Medical Services at the 2nd Africa Climate Summit
Posted On: 8 Sep 2025
Congratulations, Dr. Megersa Alemu!
Posted On: 29 Aug 2025
An oxygen production center is under construction at Eka Kotebe Hospital.
Posted On: 17 Aug 2025
.png)