News detail
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በ ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል እና ኒውሮ ሳይንስ ድጋፋዊ ጉብኝት አካሄዱ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት የባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል እና ኒውሮ ሳይንስ ተቋም በመገኘት ከሆስፒታሉ ሀላፊዎች ጋር በመሆን በሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የተቋቋሙን እድሳት የሚገኝበት ሁኔታ ላይ የመሰክ ምልከታ አካሂደዋል።
በጉብኝቱ ላይ የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር ሙሉቀን ተስፋየ እንግዶቹን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ የተለያዩ የሆስፒታሉ የህክምና አገልግሎት መስጫ ቦታዎችን፣ በተቋሙ ውስጥ እየተከናወነ ያለውን እድሳት አስጎብኝተዋል።
በሆስፒታሉ በተደረገ ምልከታ ሆስፒታሉ ከአገልግሎት አሰጣጥ አንጻር ጥሩ የሚባል ስራ እየሰራ እንዳለ ለማየት ተችሏል። በተለየም ለሆስፒታሉ የስረዓት ማነቆዎችን በመለየት፣ የመፍትሔ ሃሳብ በማስቀመጥ ከዚህም በተጨማሪም የተጠቃሚዎች እርካታ ዳሰሳ በማድረግ ለተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ለማሻሻል የተሄደበት መንገድ አመርቂ መሆኑን ማየት ተችሎአል።
በሌላ በኩል የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ እንደገለፁት ፦የተጀመረው ሆስፒታሉን በቴክኖሎጂ የማዘመን ስራንአጠናክሮከዳር ማድረስ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን አክለውም አሁን ያላቹት አመራሮች በያዛችሁት ስልታዊና የአገልግሎት ጥራት ላይ ትኩረት ያደረገ አመራር : ሆስፒታሉን ወደአለማችሁት የላቀ ደረጃ እንደምታደርሱት ሙሉ እምነቴ ነው የእኛም ድጋፍ ከጎናችሁ ነውብለዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ ከጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ አባላት እጅግገንቢ አስተያየት ሰተዋል። ላቀረቡት ጥያቄዎችም ከሆስፒታሉ የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል።የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት የባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ላደረጋችሁልን ገንቢ ድጋፋዊ ጉብኝት በሆስፒታሉ ስም ልባዊ አክብሮታችንን እንገልፃለን።
Latest News
Eka Kotebe Hospital Provides Emergency Medical Services at the 2nd Africa Climate Summit
Posted On: 8 Sep 2025
Congratulations, Dr. Megersa Alemu!
Posted On: 29 Aug 2025
An oxygen production center is under construction at Eka Kotebe Hospital.
Posted On: 17 Aug 2025
.png)